የእርስዎ ደህንነት

የእርስዎ ደህንነት በምናደርገው ነገር ሁሉ ቅድሚያ ይሰጠዋል።

የእርስዎ ውሂብ ደህንነት ካልተጠበቀ የግል ውሂብ አይደለም ማለት ነው። ለዚህ ነው እንደ ፍለጋ፣ ካርታዎች እና YouTube ያሉ የGoogle አገልግሎቶች በጣም ከተራቀቁ የዓለም የደህንነት መሠረተ ልማቶች ውስጥ በአንዱ የሚጠበቁ መሆናቸውን የምናረጋግጠው።

ምሥጠራ የእርስዎ ውሂብ በሽግግር ላይ ሳለ የግል እንደሆነ እንዲቆይ ያደርጋል

ምሥጠራ ከፍተኛ የሆነ የደህንነት እና የግላዊነት ደረጃ ለአገልግሎቶቻችን ይሰጣቸዋል። እርስዎ እንደ ኢሜይል መላክ፣ ቪዲዮ ማጋራት፣ የድር ጣቢያ መጎብኘት ወይም የእርስዎን ፎቶዎች ማከማቸት ያሉ ነገሮችን በሚያደርጉበት ጊዜ የሚፈጥሩት ውሂብ በእርስዎ መሣሪያ፣ የGoogle አገልግሎቶች እና የውሂብ ማዕከሎቻችን መካከል ይንቀሳቀሳል። የምስጠራ ቴክኖሎጂ መሪ የሆኑትን ኤችቲቲፒኤስ እና የመጓጓዣ ንብርብር ደህንነትን ጨምሮ ይህን ውሂብ በበርካታ ድርብርብ የደህንነት እንጠብቀዋለን።

የእኛ የደመና መሠረተ ልማት የእርስዎን ውሂብ በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀናት ጥበቃ ያደርግለታል

በብጁ ንድፍ ከተነደፉ የውሂብ ማዕከላት ጀምሮ እስከ በአህጉራት መካከል ውሂብን የሚያሸጋግሩ የባሕር ስር የፋይበር ገመዶች ድረስ Google በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉ ደህንነታቸው በጣም ከተጠበቁ እና አስተማማኝ የደመና መሠረተ ልማቶች ከሆኑት ውስጥ በአንዱ ስራውን ያከናውናል። እንዲሁም የእርስዎን ውሂብ ለመጠበቅ እና በሚያስፈልገዎት ጊዜ የሚገኝ እንዲሆን ለማድረግ ቀጣይነት ባለው መልኩ ቁጥጥር ይደረግበታል። እንዲያውም፣ ውሂብ በበርካታ የውሂብ ማዕከሎች ላይ እናሰራጫለን፣ ስለዚህ እሳት ወይም አደጋ የተከሰተ እንደሆነ በራስ-ሰር እና ያለምንም ችግር ወደ የረጉ እና ደህንነታቸው ወደተጠበቁ አካባቢዎች መሸጋገር ይችላል።

ስጋትን ፈልጎ ማግኛ አገልግሎቶቻችን እንዲጠበቁ ያግዛል

የእኛን አገልግሎቶች እና ከስር ያሉ መሠረተ ልማቶችን ስጋቶች፣ አይፈለጌ መልዕክት፣ ተንኮል-አዘል ዌር፣ ቫይረሶች እና ሌሎች ተንኮል አዘል ኮድ ዓይነቶችን ጨምሮ ከአደጋዎች ለመጠበቅ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንከታተላቸዋለን።

ቀጥተኛ የውሂብዎ መዳረሻ ለመንግሥታት አንሰጥም

የውሂብዎን ወይም የእርስዎን ውሂብ የሚያከማቹ የአገልጋዮቻችን የ«ጓሮ በር» መዳረሻን በጭራሽ አንሰጥም፣ አራት ነጥብ። ይህም ማለት ማንኛውም መንግስታዊ አካል፣ የአሜሪካም ሆነ የሌላ፣ ወደ የተጠቃሚዎችን መረጃ ቀጥተኛ መዳረሻ የለውም ማለት ነው። የተጠቃሚ ውሂብን እንድንሰጥ በሕግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች የምንጠየቅባቸው ጊዜያት አሉ። የሕግ ክፍል ቡድናችን እነዚህን ጥያቄዎች ይገመግማል፣ እና አንድ ጥያቄ በጣም ሰፊ ወይም ትክክለኛውን ሂደት ያልተከተለ ሆኖ ሲገኝ ጥያቄውን ይከላከለዋል። በእኛ የግልጽነት ሪፖርት ላይ ስለነዚህ የውሂብ ጥያቄዎች ግልጽ ለመሆን በጣም ጠንክረን ሠርተናል።

ምሥጠራ ከአይፍል ታወር ፎቶ ውጭ ይዘልቃል

የGmail ምሥጠራ የኢሜይሎች ግላዊነትን ይጠብቃል

ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ Gmail እርስዎ የሚልኩትን ነገሮችን መጥፎ ሰዎች እንዳያነብቡ ከባድ የሚያደርግባቸውን የምሥጠራ ግንኙነቶችን ይደግፋል። እንዲሁም Gmail እንደ ባልተመሰጠረ ግንኙነት ላይ የተላከ ኢሜይል በሚቀበሉበት ጊዜ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነትት ስጋቶችን በተመለከተ ያስጠነቅቀዎታል።

የGmail ኢሜይል ፖስታ የደህንነት ቅኝት ማስጠንቀቂያ ምልክትን ያዘጋጃል

የGmail አይፈለጌ መልዕክት ጥበቃ አጠራጣሪ ኢሜይሎችን አጣርቶ ያወጣል

ብዙ የተንኮል-አዘል ዌር እና የማስገር ጥቃቶች የሚጀምሩት በኢሜይል ነው። የGmail ደህንነት ከሌላ ማንኛውም የኢሜይል አገልግሎት በተሻለ መልኩ እርስዎን ከአይፈለጌ መልዕክት፣ ማስገር እና ተንኮል-አዘል ዌር ይጠብቀዎታል። Gmail ተጠቃሚዎች እንደ አይፈልጌ መልዕክት ምልክት ያደረጉባቸውን የኢሜይሎች ባህሪዎች ለይቶ ለማወቅ በቢሊዮኖች ከሚቆጠሩ የተወሰዱ ሥርዓተ ጥለቶችን ይተነትናል፣ በመቀጠልም አጠራጣሪ ወይም አደገኛ ኢሜይሎች ወደ እርስዎ ከመድረስዎ በፊት ለማገድ እነዚያን ምልክቶችን ይጠቀምባቸዋል። ለሚቀበሏቸው አጠራጣሪ ኢሜይሎች «አይፈልጌ መልዕክት ሪፖርት አድርግ» የሚለውን በመምረጥ ሊያግዙ ይችላሉ።

የማሽን መማር እና ሰው ሰራሽ አእምሮ የGmail አይፈልጌ መልዕክት ማጣሪያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትክክል እንዲሆኑ ያግዛሉ። በአሁኑ ጊዜ 99.9% ያህል አይፈልጌ መልዕክት ወደ መልዕክት ገቢ ሳጥንዎ እንዳይደርሱ ይጠብቃል።

የChrome አሳሽ ከደህንነት ዝማኔ ግስጋሴ ጋር

Chrome የአሳሽዎን ደህንነት በራስ-ሰር ያዘምናል

የደህንነት ቴክኖሎጂዎች ሁልጊዜ በመለዋወጥ ላይ ናቸው፣ ስለዚህ ደህንነትን ጠብቆ መቆየት ማለት እንደተዘመኑ መቆየት ማለት ነው። ለዚህም ሲባል Chrome እየተጠቀሙ ያሉት አሳሽ ስሪት ከቅርብ ጊዜው ደህንነት ማስተካከያዎች፣ ከተንኮል-አዘል ዌርና ከአታላይ ጣቢያዎች ጥበቃዎች እና በመሳሰሉት ጥበቃ መዘመኑን በመደበኛነት ይፈትሻል። Chrome በራስ-ሰር ስለሚዘምን የቅርብ ጊዜው የChrome ደህንነት ቴክኖሎጂ እርስዎን ይጠብቃል።

ጎጂ መተግበሪያ ወደ መሣሪያ ሾልኮ ይገባል

Google Play ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ መተግበሪያዎች ወደ የእርስዎ ስልክ እንዳይደርሱ ያደርጋል

አንዱ የመሣሪያዎ ትልቁ የደህንነት ተጋላጭነት የሚጭኑበት መተግበሪያ ሊሆን ይችላል። የእኛ ፈልጎ ማግኛ ሥርዓት ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጎጂ መተግበሪያዎች Play መደብር ገና ከመድረሳቸው በፊት ይጠቁማቸዋል። አንድ መተግበሪያ ደህንነቱ አስተማማኝ እንደሆነ እርግጠኛ ካልሆነን በAndroid የደህንነት ጥበቃ ቡድን አባላት ራሳቸው ይገመገማል። የፈልጎ ማግኛ ሥርዓታችን እያሻሻልን ስንሄድ በGoogle Play ላይ አስቀድመው ያሉ መተግበሪያዎችን ዳግም እንመዝናቸዋለን፣ እንዲሁም ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉትን በእርስዎ መሣሪያ ላይ እንዳይደርሱ እናስወግዳቸዋለን።

Google ተንኮል-አዘል እና አሳሳች ማስታወቂያዎችን ያግዳል

የእርስዎ የመስመር ላይ ተሞክሮ ተንኮል-አዘል ዌር በሚሸከሙ ማስታወቂያዎች፣ ለማየት የሚሞክሩትን ይዘት በሚሸፍኑ፣ የሐሰት ምርቶችን በሚያስተዋውቁ ወይም አለበለዚያ የማስታወቂያ መመሪያዎቻችንን በሚጥሱ ማስታወቂያዎች ሊበላሽ ይችላል። ይህን ችግር በጣም አክብደን ነው የምናየው። በየዓመቱ ቀጥተኛ ገምጋሚዎቻችን እና የተራቀቀ ሶፍትዌራችን ወደ አንድ ቢሊዮን የሚጠጉ መጥፎ ማስታወቂያዎችን ያግዳሉ። በተጨማሪም የሚያስከፉ ማስታወቂያዎችን ሪፖርት እንዲያደርጉ እና የሚመለከቷቸውን ማስታወቂያ ዓይነቶች መቆጣጠር የሚችሉባቸውን መሣሪያዎች እንሰጠዎታለን። እናም በይነመረቡ ለሁሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ግንዛቤዎቻችንን እና ምርጥ ልምዶቻችን በንቃት እናትማለን።

የGoogle ደህንነት ጋሻ እና የማረጋገጫ ዝርዝር

የመለያዎን ደህንነት በደህንነት ፍተሻ ይጠብቁት

የGoogle መለያዎን ለመጠበቅ ማድረግ የሚችሉት የመጀመሪያ ነገር የደህንነት ፍተሻውን ማድረግ ነው። የመልሶ ማግኛ መረጃዎ የተዘመነ መሆኑን እና ከመለያዎ ጋር የተገናኙ ድር ጣቢያዎች፣ መተግበሪያዎች እና መሣሪያዎች አሁንም የሚጠቀሙባቸው እና የሚያምኗቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ስንል ገንብተነዋል። የሆነ ነገር አጠራጣሪ ከመሰለ ቅንብሮችዎን ወይም የይለፍ ቃልዎን ወዲያውኑ መቀየር ይችላሉ። የደህንነት ፍተሻ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድ ሲሆን የፈለጉትን ያህል ጊዜ ደጋግመው ማድረግ ይችላሉ።

የደህንነት ፍተሻውን ያድርጉ
Gmail የአጠራጣሪ እንቅስቃሴ ማንቂያ ይቀበላል

ስለአጠራጣሪ እንቅስቃሴ ማንቂያዎችን ያግኙ

መለያዎን ከመጥፎዎቹ ሰዎች ለመጠበቅ ከያልተለመደ እንቅስቃሴ እንዳይኖር እንከታተላለን፣ እና የሆነ ነገር ትክክል ካልመሰለ እናሳውቀዎታለን። ለምሳሌ፣ አንድ ያልታወቀ መሣሪያ ወደ መለያዎ ለመግባት ከሞከረ ወይም የመለያዎ መልሶ ማግኛ መረጃ ከተቀየረ ይህ እንቅስቃሴ የእርስዎ መሆኑን ለማረጋገጥ ወዲያውኑ እርስዎን እናገኛለን። ማሳወቂያዎች ለእርስዎ በኢሜይል ይላኩልዎታል ነገር ግን በእርስዎ ስልክ ላይ የጽሑፍ መልእክቶችን ለመቀበል በተጨማሪ መመዝገብ ይችላሉ።

በተመሳሳዩ የማረጋገጫ ኮድ የመሣሪያ እና የአሳሽ ወደ መለያ መግባት

ጥቃቶችን ለመከላከል የእርስዎን በመለያ-መግባት ያጠንክሩ

ጠንካራ የይለፍ ቃል ሰርጎገቦችን ይከላከላል፣ እና መለያዎን ይጠብቃል። ጥሩ የይለፍ ቃል ለመፍጠር ልዩ መሆኑን፤ የፊደሎች፣ ቁጥሮች እና ምልክቶች ድብልቅ መያዙን እና Google ላይ ብቻ የሚጠቀሙበት መሆኑን ያረጋግጡ።

እንዲሁም ባለ2-ደረጃ ማረጋገጫን በማቅረብ የመለያዎ ደህንነቱ ይበልጥ የተጠበቀ እንዲሆን እንዲያደርጉ እናግዛለን። በባለ2-ደረጃ ማረጋገጫ አማካኝነት ወደ የእርስዎ መለያ ለመግባት ከይለፍ ቃልዎ በላይ ያስፈልጋል። ይሄ ወደ የእርስዎ ስልክ የተላከው ባለስድስት አሃዝ ኮድ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ደግሞ ከማስገር የበለጠ ለመጠበቅ ወደ የእርስዎ ኮምፒውተር ዩኤስቢ ወደብ ያስገቡት የደህንነት ቁልፍ ሊሆን ይችላል።

አሳሽ በChrome ውስጥ የሚጠበቁ የይለፍ ቃላትን ያሳያል

ራስዎን በእነዚህ የይለፍ ቃል ደህንነት መጠበቂያ መሣሪያዎች ይጠብቁ

የChromeን አብሮገነብ የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ ለተለያዩ የድር ጣቢያዎች እንዲያስታውስ መፍቀድ ጠንካራና ልዩ የሆኑ የይለፍ ቃላትን ለእያንዳንዱ ጣቢያ እንዲጠቀሙ ቀላል ያደርግልዎታል። በተጨማሪም የእርስዎን የGoogle ይለፍ ቃል የGoogle ባልሆነ ጣቢያ ላይ በሚያስገቡበት ጊዜ የአስጋሪ ጥቃቶችን እንዲያስቀሩ የሚያግዘዎት የChrome ቅጥያ የሆነው የይለፍ ቃል ማንቂያን ማከል ይችላሉ።

Google ካርታዎች በአሳሽ ላይ ከሩቅ የተቆለፈን የጠፋ ስልክ ያለበትን ቦታ ያገኛል

ስልክዎ በሚጠፋብዎት ጊዜ የመለያዎን ደህንነት ይጠብቁ

የእርስዎ ስልክ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ የእርስዎን ውሂብ በጥቂት ፈጣን እርምጃዎች መጠበቅ እንዲችሉ የእኔ መለያን ይጎብኙ። ያለዎት መሣሪያ የAndroid ወይም iOS ይሁን ያለበትን ማወቅ እና መቆለፍ፣ የይለፍ ቃልዎን መቀየር፣ በመነሻው ገጽ ላይ ብጁ መልዕክት ማከል ወይም ሌላው ሳይቀር በእርስዎ ስልክ ላይ ያለውን ውሂብ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ ይችላሉ።