ይቆጣጠሩ

እርስዎ ግላዊነትዎን ማቀናበር የሚችሉባቸው መቆጣጠሪያዎች አለዎት።

ውሂብን የእኛን አገልግሎቶች በተቻለ መጠን ጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እንጠቀምበታለን፣ ሆኖም ግን ምን ዓይነት ውሂብ እንደምንሰበስብ እና እንደምንጠቀም እርስዎ ነዎት የሚወስኑት። የእርስዎን ግላዊነት እና ደህንነት እንዲያስተዳድሩ የሚያግዙና ለመጠቀም ቀላል የሆኑ የመሣሪያዎች ፈጣን መዳረሻ የሚሰጥዎትን የእኔ መለያ ገንብተናል። የሚከተሉትን ቅንብሮች በመገምገም የእርስዎ ውሂብ እንዴት የGoogle አገልግሎቶች ለእርስዎ የተሻለ ማድረግ እንደሚችል እርስዎ ነዎት የሚወስኑት።

ወደ የእኔ መለያ ሂድ

የግላዊነት ቅንብሮችዎን በግላዊነት ፍተሻው ያቀናብሩ

በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ Google የሚሰበስበውን የውሂብ ዓይነቶች፣ ምን ዓይነት መረጃ ለጓደኛዎች እንደሚያጋሩ ወይም ይፋዊ እንደሚያደርጉ፣ እና Google እንዲያሳየዎት የሚፈልጓቸውን የማስታወቂያዎች ዓይነት ማስተዳደር ይችላሉ። እነዚህን ቅንብሮች የፈለጉትን ያህል ጊዜ በመደጋገም መቀየር ይችላሉ።

የግላዊነት ፍተሻውን ያድርጉ

የመለያዎን ደህንነት በደህንነት ፍተሻ ይጠብቁት

የGoogle መለያዎን ለመጠበቅ ማድረግ የሚችሉት የመጀመሪያ ነገር የደህንነት ፍተሻውን ማድረግ ነው። የመልሶ ማግኛ መረጃዎ የተዘመነ መሆኑን እና ከመለያዎ ጋር የተገናኙ ድር ጣቢያዎች፣ መተግበሪያዎች እና መሣሪያዎች አሁንም የሚጠቀሙባቸው እና የሚያምኗቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ስንል ገንብተነዋል። የሆነ ነገር አጠራጣሪ ከመሰለ ቅንብሮችዎን ወይም የይለፍ ቃልዎን ወዲያውኑ መቀየር ይችላሉ። የደህንነት ፍተሻ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድ ሲሆን የፈለጉትን ያህል ጊዜ ደጋግመው ማድረግ ይችላሉ።

የደህንነት ፍተሻውን ያድርጉ

ምን ውሂብ ከእርስዎ መለያ ጋር እንደሚጎዳኝ ይወስኑ

በካርታዎች ውስጥ ካሉ ከተሻሉ የመጓጓዣ አማራጮች ጀምሮ እስከ በፍለጋ ውስጥ ይበልጥ ፈጣን ውጤቶች ድረስ በመለያዎ ላይ የምናስቀምጠው ውሂብ የGoogle አገልግሎቶች ለእርስዎ ይበልጥ ጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ይችላል። የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎችን በመጠቀም ከመለያዎ ጋር ምን እንደሚጎዳኝ መምረጥ እና የተወሰኑ ውሂብ ዓይነቶችን ማሰባሰብ — እንደ የእርስዎ ፍለጋዎች እና የአሰሳ እንቅስቃሴ፣ የሚሄዱባቸው ቦታዎች እና ከእርስዎ መሣሪያዎች የሚገኝ መረጃን ያሉ — ለአፍታ ማቆም ይችላሉ።

ወደ የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች ይሂዱ

በእርስዎ ምርጫዎች ላይ በመመስረት ማስታወቂያዎችን ይቆጣጠሩ

በእርስዎ የማስታወቂያ ቅንብሮች ውስጥ እርስዎ በሚፈልጓቸው ርዕሶች ላይ በመመስረት ማስታወቂያዎችን መቆጣጠር ይችላሉ። ለምሳሌ፦ ለGoogle እርስዎ ፖፕ ሙዚቃን እንደሚወዱ ለመንገር የማስታወቂያዎች ግላዊነት ማላበሻ ቅንብሮችን ከተጠቀሙ እርስዎ ወደ YouTube ሲገቡ ወደፊት ስለሚለቀቁ እና በአቅራቢያዎ ስላሉ የትዕይንት ዝግጅቶች በተመለከተ ማስታወቂያዎችን ሊመለከቱ ይችሉ ይሆናል።

ወደ መለያ ገብተው ሳለ የማስታወቂያዎች ግላዊነት ማላበሻን ካጠፉ በመላ የGoogle አገልግሎቶች እና ድር ጣቢያዎች እንዲሁም ከእኛ ጋር አጋር በሆኑ መተግበሪያዎች ላይ ከእርስዎ ፍላጎት ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ማሳየት እናቆማለን። ዘግተው የወጡ ከሆነ የማስታወቂያዎች ግላዊነት ማላበሻን ማጥፋት ማስታወቂያዎች የሚታዩባቸው የGoogle አገልግሎቶች ላይ ብቻ ነው ተጽዕኖ የሚያሳርፈው።

ወደ የማስታወቂያዎች ቅንብሮች ይሂዱ

በየእኔ እንቅስቃሴ ላይ በእርስዎ መለያ ውስጥ ምን ውሂብ እንዳለ ይመልከቱ

የእኔ እንቅስቃሴ እርስዎ የፈለጓቸውን፣ የተመለከቷቸውን እና አገልግሎቶቻችን በመጠቀም የተመለከቷቸውን ነገሮች ማግኘት የሚችሉበት ማእከላዊ ቦታ ነው። ያለፈ የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎን ማስታወስ ቀላል ለማድረግ በርዕሶች፣ ቀን እና ምርት የሚፈልጉባቸውን መሣሪያዎች እንሰጠዎታለን። የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ወይም ሌላው ሳይቀር ከእርስዎ መለያ ጋር እንዲጎዳኙ የማይፈልጓቸውን ሙሉ ርዕሶች በቋሚነት መሰረዝ ይችላሉ።

ወደ የእኔ እንቅስቃሴ ይሂዱ

መሠረታዊ የመለያ መረጃዎን ይገምግሙ

በGoogle አገልግሎቶች ላይ ምን የግል መረጃ — ማለትም እንደ የእርስዎ ስም፣ ኢሜይል አድራሻ እና ስልክ ቁጥር ያሉ — እንደሚያጋሩ ይቆጣጠሩ።

የግል መረጃዎን ይገምግሙ

«ውሂብዎን ያውርዱ»ን በመጠቀም የእርስዎን ይዘት ወደ የፈለጉበት ቦታ ይዘውት ይሂዱ

የእርስዎ ፎቶዎች። የእርስዎ ኢሜይሎች። የእርስዎ እውቂያዎች። እንዲያውም የእርስዎ ዕልባቶች ጭምር። በGoogle መለያዎ ላይ የተከማቸው የይዘት ተቆጣጣሪ እርስዎ ነዎት። ለዚህ ነው የእርስዎን «ውሂብዎን ያውርዱ»ን የፈጠርነው — በዚህም ቅጂ መስራት፣ ምትኬ ማስቀመጥ ወይም እንዲያውም ወደ ሌላ አገልግሎት መውሰድ ይችላሉ።

ወደ «ውሂብዎን ያውርዱ» ይሂዱ