ደህንነቱ ይበልጥ የተጠበቀ በይነመረብ

በይነመረቡ ለሁሉም ሰው ደህንነቱ አስተማማኝ እንዲሆን ለማድረግ እናግዛለን።

የእኛን ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆን መላውን የመስመር ላይ ዓለም ጭምር የሚጠቅም የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂ የመገንባት ረዥም ታሪክ አለን። የአገልግሎቶቻችን ደህንነት እንደተጠበቀ ለማቆየት ቴክኖሎጂ ስንፈጥር ለእያንዳንዱ ሰው በሚጠቅም መልኩ የምናጋራቸው ጥሩ ዕድሎችን እናገኛለን። ስጋቶች በጊዜ ሂደት እየተለዋወጡ እንደመሄዳቸው መጠን የእኛ ከጊዜው ጋር የሚሄድ እንደሁኔታው የሚለዋወጥ ወደፊት ተራማጅ የሆኑ እርምጃዎች ሌሎች ኩባንያዎች አርአያነታችንን እንዲከተሉ መንገዱን ይጠርግላቸዋል።

የጥንቃቄ አሰሳ ከChrome ተጠቃሚዎችን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይጠብቃል

የጥንቃቄ አሰሳ ቴክኖሎጂያችን መጀመሪያ የገነባነው የChrome ተጠቃሚዎችን አደገኛ ድር ጣቢያዎችን ለመጎብኘት በሚሞክሩበት ጊዜ ማንቂያዎችን በማቅረብ ከተንኮል-አዘል ዌር እና ከማስገር ሙከራዎች ለመጠበቅ ነበር። በይነመረቡ ለሁሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ይህ ቴክኖሎጂያችን Apple Safariን እና Mozilla Firefoxን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶች በምርታቸው ውስጥ እንዲጠቀሙበት በነጻ አቅርበናል። ዛሬ ግማሹ የዓለም የመስመር ላይ ሕዝብ በጥንቃቄ አሰሳ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የድር ጣቢያ ባለቤቶች ጣቢያዎቻቸው የደህንነት ግድፈቶች ሲኖርባቸው እናነቃቸዋለን፣ እንዲሁም ችግሮቹን በፍጥነት እንዲያስተካሉ የሚያግዟቸውን መሣሪያዎች በነጻ እናቀርባለን። አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂን ልክ እንደገነባን ማጋራቱን በመቀጠል ለሁሉም ሰው ለደህንነት አስተማማኝ የሆነ በይነመረብ እንዲገነባ እናግዛለን።

እርስዎ በይነመረቡን በሚያስሱበት ጊዜ ደህንነትዎ እንደተጠበቀ እንዲቆዩ ለማድረግ ኤችቲቲፒኤስ እንጠቀማለን።

ኤችቲቲፒኤስ ምሥጠራ ከአገልግሎታችን ጋር መገናኘት እርስዎ የሚፈልጉትን ነገር ብቻ እና በፈለጉበት ጊዜ ብቻ መድረስ እንዲችሉ ከሚሰልሉ ዓይኖች እና ተንኮለኛ ሰርጎገቦች ይጠብቀዎታል። ድር ጣቢያዎች ይህን ተደራቢ ደህንነት እንዲቀበሉት ለማነሳሳት የGoogle ፍለጋ ስልተ-ቀመር በፍለጋ ውጤቶቻችን ላይ ለድር ጣቢያዎች ደረጃ ሲሰጥ የኤችቲቲፒኤስ ምሥጠራን እንደ አንድ መለኪያ ይጠቀማል።

የስጋት ተጋላጭነቶችን ማጋለጥ እንዲቻል የደህንነት ሽልማቶችን እንፈጥራለን

Google ላይ የግል ተመራማሪዎች በአገልግሎታችን ላይ ተጋላጭነቶችን እንዲያገኙና የደህንነት ጥገናዎችን እንዲፈጥሩ ገንዘብ የሚከፍሉ የደህንነት ሽልማት ፕሮግራሞችን እንፈጥራለን። በየዓመቱ በምርምር የገንዘብ ስጦታዎች እና የሳንካ ጥገና ሽልማቶች ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን በሽልማት እንሰጣለን። በአሁኑ ጊዜ እንደ Chrome እና Android ላሉ አብዛኛዎቹ የGoogle ምርቶች የደህንነት ሽልማት ፕሮግራሞችን እንጠቀማለን።

የደህንነት መሣሪያዎቻችን ለገንቢዎች የሚገኙ እናደርጋለን

የደህንነት ቴክኖሎጂያችን ለሌሎች ዋጋ ይኖረዋል ብለን ስናምን እናጋራዋለን። ለምሳሌ፣ ገንቢዎች የድር መተግበሪያዎቻቸው በApp Engine ውስጥ የደህንነት ተጋላጭነቶች ካላቸው መፈተሽ እንዲችሉ Google የደመና ደህነንት ቃኚ በነጻ የሚገኝ እናደርግላቸዋለን።

ደህንነቱ ይበልጥ አስተማማኝ የሆነ በይነመረብን ለማጎልበት የልምዳችን ውሂብን እናጋራለን።

ከ2010 ጀምሮ Google እንደ የቅጂ መብት ማስወገዶች፣ መንግሥት እንዲሰጠው የሚጠይቀው የተጠቃሚ ውሂብ ጥያቄዎች እና እንደ የጥንቃቄ አሰሳ ያሉ ስታቲስቲክስን ለይተው የሚያቀርብ የግልጽነት ሪፖርት አትሟል። በተጨማሪም፣ ኢንዱስትሪው የድር ጣቢያዎች እና የኢሜይል ምሥጠራ አቀባበሉ ላይ ውሂብ እናጋራለን። ይህን የምናደርገው ግስጋሴያችን ለተጠቃሚዎቻችን ለማጋራታ ብቻ ሳይሆን ደህንነቱ ይበልጥ ለተጠበቀ በይነመረብ ለሁሉም ሰው ለማኖር ሲባል ሌሎች ይበልጥ ጠንካራ የደህንነት መስፈርቶችን እንዲቀበሉ ለማበረታታት ነው።