ማስታወቂያዎች እንዴት ነው የሚሰሩት

የግል መረጃዎን ለማንም አንሸጥም።

አብዛኛው ንግዳችን በሁለቱም የGoogle አገልግሎቶች እና ከእኛ ጋር አጋርነት በፈጠሩ ድር ጣቢያዎች እና ሞባይል መተግበሪያዎች ላይ ማስታወቂያዎችን በማሳየት ላይ የተመሠረተ ነው። ማስታወቂያዎች አገልግሎቶቻችን ለሁሉም ሰው ነጻ እንዲሆኑ ያግዛሉ። እነዚህን ማስታወቂያዎች ለእርስዎ ለማሳየት ውሂብ እንጠቀማለን፣ ሆኖም ግን እንደ የእርስዎ ስም፣ ኢሜይል አድራሻ እና የክፍያ መረጃ ያለ የግል መረጃን አንሸጥም።

ማስታወቂያዎች ተዛማጅነት ያላቸው እንዲሆኑ ለማድረግ ውሂብን እንጠቀማለን

የእርስዎ ፍለጋዎች እና አካባቢዎች፣ የተጠቀሙባቸው ድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች፣ የተመለከቷቸው ቪዲዮዎች እና ማስታወቂያዎች እንዲሁም እንደ የእርስዎ ዕድሜ ክልል፣ ጾታ እና የፍላጎት ርዕሶች ያሉ እርስዎ የሰጡን የግል መረጃን ጨምሮ ከመሣሪያዎችዎ ላይ የተሰበሰበ ውሂብን በመጠቀም ጠቃሚ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት እንሞክራለን።

ወደ መለያ ገብተው ከሆነና በእርስዎ የማስታወቂያዎች ቅንብሮች የሚወሰን ሆኖ ይህ ውሂብ በእርስዎ መሣሪያዎች ዙሪያ ለሚያዩዋቸው ማስታወቂያዎች መረጃ ይሰጣል። በሥራ ቦታዎ ኮምፒውተር ላይ የጉዞ ድር ጣቢያን ከጎበኙ በዚያን ቀን ምሽት ላይ በእርስዎ ስልክ ላይ ወደ ፓሪስ ስላሉ የአይሮፕላን በረራ ዋጋዎችን የሚመለከቱ ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ።

ማስታወቂያ ሰሪዎች ሰዎች ለተመለከቷቸው ወይም መታ ላደረጓቸው ማስታወቂያዎች ብቻ ነው የሚከፍሉት

ማስታወቂያ ሰሪዎች ከእኛ ጋር የማስታወቂያ ዘመቻዎችን ያካሄዳሉ፣ እነዚያ ማስታወቂያዎች በትክክለኛ አፈጻጸማቸው መሠረት ብቻ ነው የሚከፍሉን — እንጂ በእርስዎ የግል መረጃ ላይ ተመስርተው በጭራሽ አይከፍሉንም። ይሄ እያንዳንዱ ሰው አንድን ማስታወቂያ በተመለከተ ወይም መታ ባደረገ ቁጥር፣ ወይም እንደ አንድን መተግበሪያ ማውረድ ወይም የጥያቄ ቅጽን መሙላት ያለ ማስታወቂያን ከተመለከተ በኋላ ድርጊትን ባከናወነ ቁጥር ሊያካትት ይችላል።

የማስታወቂያ ሰሪዎች ዘመቻዎች እንዴት እንደሠራላቸው እንነግራቸዋለን

ማስታወቂያ ሰሪዎች ስለማስታወቂያዎቻቸው አፈጻጸም መረጃ እንሰጣቸዋለን፣ ነገር ግን ይህን የምናደርገው ምንም የግል መረጃዎን ሳናሳይ ነው። ለእርስዎ ማስታወቂያዎችን በማሳየት ሂደት ላይ ባለው እያንዳንዱ ነጥብ ላይ የእርስዎን የግል መረጃ እንደተጠበቀ እና የግል ጉዳይ እንደሆነ እናቆየዋለን።

ማስታወቂያዎች እንዴት በGoogle አገልግሎቶች እና የአጋር ጣቢያዎች ላይ እንደሚሠሩ

በGoogle አገልግሎቶች ላይም ሆነ ከእኛ ጋር አጋርነት በፈጠሩ ድር ጣቢያዎችና ሞባይል መተግበሪያዎች ላይ ለእርስዎ ጠቃሚ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ውሂብን እንጠቀማለን።

በአሳሽ መስኮት ውስጥ የተለያየ ቀለም ያላቸው ብስክሌቶች

የፍለጋ ማስታወቂያዎች እንዴት እንደሚሠሩ

እርስዎ Google ፍለጋን ሲጠቀሙ ማስታወቂያዎች ተዛማጅነት ካላቸው ውጤቶች አጠገብ ወይም ከላይ ብቅ ሊሉ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ማስታወቂያዎች እርስዎ ባከናወኑት ፍለጋ እና እርስዎ ባሉበት አካባቢ የሚነቃቁ ናቸው። ለምሳሌ፣ ለ«ቢስክሌቶች» ፍለጋ ካደረጉ በሽያጭ ላይ ያሉ ቢስክሌቶችን የተመለከቱ ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ።

በሌሎች አጋጣሚዎች የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለማቅረብ እንደ ያለፉ ፍለጋዎችዎ ወይም አስቀድመው የጎበኟቸው ጣቢያዎች ያሉ ተጨማሪ ውሂብ ይበልጥ ጠቃሚ እንጠቀማለን። አስቀድመው «ቢስክሌቶች»ን እንደመፈለግዎ አሁን ደግሞ «ሽርሽር» ብለው ከፈለጉ በሽርሽር ጊዜዎ ላይ ሳሉ በቢስክሌት ለመሄድ የሚችሉባቸው ቦታዎችን የተመለከቱ ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ።

Google ማስታወቂያዎች በGmail ውስጥ በቢጫ እንዲደምቁ ተደርገው

የYouTube ማስታወቂያዎች እንዴት እንደሚሠሩ

በYouTube ላይ ቪዲዮዎችን ሲመለከቱ ቀደም ብለው ወይም በቪዲዮ ገጹ ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ። እነዚህ ማስታወቂያዎች በYouTube ላይ በተመለከቷቸው ቪዲዮዎች እና የአሁኑ እና የቅርብ ጊዜ የYouTube ፍለጋዎችዎን ጨምሮ በሌሎች በሌላ ውሂብ ላይ የተመሠረቱ ናቸው።

ለምሳሌ ለ«የፋሽን ምክሮች» ፍለጋ ካደረጉ ወይም ከውበት ጋር የተዛመዱ ቪዲዮዎችን ከተመለከቱ ለአዲስ የውበት ተከታታይ ፊልም የተዘጋጀ ማስታወቂያን ሊመለከቱ ይችሉ ይሆናል። እነዚህ ማስታወቂያዎች የሚመለከቷቸው ቪዲዮዎች ፈጣሪዎች ለመደገፍ ያግዛሉ።

ብዙ የYouTube ማስታወቂያዎችን ማየት ካልፈለጉ ሊዘልሏቸው ይችላሉ።

የጊዜው ተፈላጊ የሆኑ የፀሐይ መነጽሮች ብቅ-ባይ ያለው ደስተኛ ሴት የሚያሳይ የYouTube ቪዲዮ

የGmail ማስታወቂያዎች እንዴት እንደሚሠሩ

በGmail ውስጥ የሚመለከቷቸው ማስታወቂያዎች ከGoogle መለያዎ ጋር በተጎዳኘ ውሂብ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። ለምሳሌ፣ እንደ YouTube ወይም ፍለጋ ባሉ ሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ላይ ያለው እንቅስቃሴዎ በGmail ውስጥ የሚመለከቷቸው የማስታወቂያዎች ዓይነት ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል። Google ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት በገቢ መልዕክት ሳጥንዎ ውስጥ ያሉ ቁልፍ ቃላትን ወይም መልዕክቶችን አይጠቀምም። ማንም ሰው ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ብሎ ኢሜይልዎን አያነብብም።

ቄንጠኛ የሆነ የአረንጓዴ ቦርሳ ማስታወቂያ ያለው የመገለጫ ፎቶ ያለው አሳሽ

ማስታወቂያዎች በGoogle አጋር ጣቢያዎች ላይ እንዴት እንደሚሠሩ

በርካታ ድር ጣቢያዎች እና የሞባይል መተግበሪያዎች ማስታወቂያዎችን ለማሳየት ከእኛ ጋር በአጋርነት ይሠራሉ። እነዚህ ማስታወቂያ ሰሪዎች ተጠቃሚዎች ለእኛ ባጋሩትን የግል መረጃ ላይ እና ስለመስመር ላይ እንቅስቃሴዎ በሰበሰብነው ውሂብ ላይ ተመስርተው የተወሰኑ ማስታወቂያዎችን ለታዳሚዎች «አይነቶች» ለማሳየት ይወስናሉ፦ ለምሳሌ፣ «የመጓዝ ፍላጎት ያላቸው ዕድሜያቸው ከ25 እስከ 34 የሚሆኑ ወንዶች»።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በጎበኟቸው ጣቢያዎች ላይ በመመስረት ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ እናሳየዎታለን — ለምሳሌ፣ ወደ የመስመር ላይ የመገበያያ ጋሪዎ ያከሉት፣ በኋላ ላይ ግን ላለመግዛት ስለወሰኑት ቀይ ጫማ የተመለከቱ ማስታወቂያዎችን ሊመለከቱ ይችላሉ። ሆኖም ግን ይህን የምናደርገው እንደ የእርስዎ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ ወይም የመክፈያ መረጃን ያሉ ማንኛቸውም የግል መረጃዎችን ለማንም ሳናሳይ ነው።

የGoogle ማስታወቂያዎች ተሞክሮዎን ይቆጣጠሩ

ወደ መለያዎ ገቡም አልገቡም የሚያዩዋቸውን የማስታወቂያ ዓይነቶች የሚቆጣጠሩባቸው መሣሪያዎችን እንሰጠዎታለን።

የማስታወቂያ ቅንብሮች ያለው ጡባዊ እና የፀሐይ መነጽሮች ማስታወቂያ

በእርስዎ ምርጫዎች ላይ በመመስረት ማስታወቂያዎችን ይቆጣጠሩ

በእርስዎ የማስታወቂያ ቅንብሮች ውስጥ እርስዎ ፍላጎት ባለዎት ርዕሶች ላይ በመመስረት ማስታወቂያዎችን መቆጣጠር ይችላሉ። ለምሳሌ፦ ለGoogle እርስዎ ፖፕ ሙዚቃን እንደሚወዱ ለመንገር የማስታወቂያዎች ግላዊነት ማላበሻ ቅንብሮችን ከተጠቀሙ እርስዎ ወደ YouTube ሲገቡ ወደፊት ስለሚለቀቁ እና በአቅራቢያዎ ስላሉ የትዕይንት ዝግጅቶች በተመለከተ ማስታወቂያዎችን ሊመለከቱ ይችሉ ይሆናል።

ወደ መለያ ገብተው ሳለ የማስታወቂያዎች ግላዊነት ማላበሻን ካጠፉ በመላ የGoogle አገልግሎቶች እና ድር ጣቢያዎች እንዲሁም ከእኛ ጋር አጋር በሆኑ መተግበሪያዎች ላይ ከእርስዎ ፍላጎት ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ማሳየት እናቆማለን። ዘግተው የወጡ ከሆነ የማስታወቂያዎች ግላዊነት ማላበሻን ማጥፋት ማስታወቂያዎች የሚታዩባቸው የGoogle አገልግሎቶች ላይ ብቻ ነው ተጽዕኖ የሚያሳርፈው።

ከላይ የድምጸ-ከል አዝራር ያለው የአረንጓዴ መኪና Google ማስታወቂያ

ማየት የማይፈልጓቸውን ማስታወቂያዎች ያስወግዱ

በአጋሮቻችን ድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች በኩል በምናሳያቸው አብዛኛዎቹ ማስታወቂያዎች ላይ የ«ይህን ማስታወቂያን ድምጸ-ከል አድርግበት» ችሎታ እንሰጠዎታለን። በማስታወቂያው ጥግ ላይ ያለውን «X» በመምረጥ ከአሁን በኋላ ተገቢ ሆነው የማያገኟቸውን ማስታወቂያዎች ማስወገድ ይችላሉ።

ለምሳሌ፣ አዲስ መኪና ለመግዛት እየፈለጉ ሳሉ የመኪና ማስታወቂያዎች ጠቃሚ ሆነው ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን አንዴ አዲስ መኪና ገዝተው በደስታ መንዳት ከጀመሩ በኋላ ስለገዙት መኪና ማስታወቂያ ዳግመኛ ማየት ላይፈልጉ ይችላሉ።

ወደ መለያ ከገቡና በእርስዎ የማስታወቂያዎች ቅንብሮች ላይ የሚወሰን ሆኖ ይህ ቁጥጥር ከእኛ አጋር በፈጠሩ ድር ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ እርስዎ በመለያ በገቡባቸው መሣሪያዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል።

እንዲሁም ማስታወቂያዎችን በሚያሳዩ በGoogle አገልግሎቶች ላይ «ይህን ማስታወቂያ ሰሪ አግድ»ን በመጠቀም ወደ መለያ መግባት ሳያስፈልገዎት ማስታወቂያዎችን ማገድ ይችላሉ።

ከላይ በስተቀኝ የመረጃ አዝራር ያለው የፀሐይ መነጽር ማስታወቂያ

ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ምን ውሂብ እንደምንጠቀም ይወቁ

ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ጥቅም ላይ የሚውለውን ውሂብ እንዲያውቁ ማገዝ እንፈልጋለን። የ«ይህ ማስታወቂያ ለምን» ባህሪ አንድን ማስታወቂያ ለምን እየተመለከቱ እንደሆኑ እንዲያውቁ ለማገዝ አንድ መጠየቂያን ጠቅ እንዲያደርጉ ያስችልዎታል። ለምሳሌ፦ የፋሽን ድር ጣቢያዎችን እየጎበኙ ስለነበረ ለቀሚስ የሚሆን ማስታወቂያን ሊመለከቱ ይችላሉ። ወይም የአንድ ምግብ ቤት ማስታወቂያን ከተመለከቱ ይህ የሆነው ባሉበት አካባቢ ምክንያት እንደሆነ ሊያውቁ ይችላሉ። እንዲህ ያለው የውሂብ ዓይነት እርስዎ ጠቃሚ ሆኖ ሊያገኟቸው ስለሚችሏቸው ነገሮች ያሉ ማስታወቂያ እንድናሳይ ያግዘናል። ነገር ግን ያስታውሱ፣ ይህን ውሂብ በጭራሽ ለማስታወቂያ ሰሪዎች አንጋራውም።